ጌትስ ኢንተርናሽናል ሕንፃ 7ኛ ፎቅ
+251-114-16-32-73
ጌትስ ኢንተርናሽናል ሕንፃ 7ኛ ፎቅ
ከ2008 እ.ኤ.አ ጀምሮ

ስለ እኛ

ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር በኦሮሚያ ክልል በወልመራ ወረዳ ከአዲስ አበባ በ35 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በምትገኘው የሆለታ ከተማ ውስጥ ይገኛል። ፋብሪካው ለዋናው የሲሚንቶ ገበያ ለአዲስ አበባ ቅርብ ሲሆን ዋና ግብዓቱ ከሚገኝበት ቦታም በመካከለኛ ርቀት ላይ ይገኛል።

ታሪካችንን

የፕሮጄክቱ ሃሳብ የመነጨው በ2008 እ.ኤ.አ ሲሆን በወቅቱ ሕዝቡ የአክሲዮን ድርሻ እንዲገዛ ቀርቦለት 16, 500 ኢትዮጵያዊያን የአክሲዮን ባለድርሻ እንዲሆኑ አድርጓል ። ፕሮጄክቱ በ2017 ዓ.ም ተመርቆ ወደስራ ገብቷል። ድርጅቱ ሁለት ጉልህ የአክሲዮን ድርሻ ያላቸው የውጭ ሃገር አጋር ተቋማት አሉት። እነዚህም ፕሪቶሪያ ፖርትላንድ ሲሜንት (PPC) እና ኢንተርናሽናል ዲቨሎፕመንት ኮርፖሬሽን ኦፍ ሳውዝ አፍሪካ ሊሚትድ (IDC) የተባሉ ድርጅቶች ሲሆኑ ሁለቱም የሚገኙት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነው።

ስለ እኛ የበለጠ

ድርጅቱ የተመሠረተበት ዓላማ በኢትዮጵያ ውስጥ በሲሚንቶ አቅርቦት እና ፍላጎት መካከል ያለውን ክፍተት መሙላት እና በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄደውን የመሠረተ-ልማት እና የቤቶች ግንባታ ሂደት በማፈጠን እገዛ ለማድረግ ጥራት ያለውን ሲሚንቶ እና ሌሎች የግንባታ ግብዓቶችን ማቅረብ ነው። በአሁኑ ወቅት ፋብሪካው ኦፒሲ (ኦሪዲናሪ ፖርትላንድ ሲሜንት) እና ፒፒሲ (ፖዞላና ፖርትላንድ ሲሜንት) የተባሉ ሁለት ዓይነት የሲሚንቶ ምርቶችን ያመርታል። በደንበኞች ፍላጎት መሠረት ተመርተው የደንበኞችን ልዩ ፍላጎቶች ማሟላት የሚችሉ አዳዲስ ምርቶችን ወደገበያው የማስገባት ዕቅዶችም አሉት። ፋብሪካው በቀን 3000 ቶን ክሊንከር እና 4500 ቶን ፒፒሲ ሲሚንቶ የማምረት አቅም አለው። ሐበሻ ሲሚንቶ የደንበኞቹን እና የባለአክሲዮኖችን ፍላጎት በማሟላት የሚያምን ሲሆን እንቅስቃሴዎቹ ሁሉ ያነጣጠሩት እነዚህን ዓላማዎች ከግብ በማድረስ ላይ ነው። ድርጅቱ ለ941 ኢትዮጵያዊ ሠራተኞች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን እነዚህም የከፍተኛ አመራርነትን ጨምሮ በተለያዩ የስራ መስኮች ተሠማርተው ይገኛሉ።

ራእይ

በዘላቂ ልማት ላይ በማተኮር እና የባለድርሻ አካላትን ፍላጎት ያማከለ በኢትዮጵያ ተቀዳሚ ምርጫ የግንባታ ግብዓቶች አምራችና አሠሪ/ ቀጣሪ ድርጅት ለመሆን

ዋና እሴቶች

ታማኝነት
ቁርጠኝነት
ግልፅነት

ተልዕኮ

በባለድርሻ አካላት የሚጠበቁ ፍላጎቶችን ለማሟላት እና በካፒታል ሥራ ላይ ከፍተኛ ትርፍ ማግኘት ፡፡
ሰራተኞቻችን አስፈላጊ ሀብቶቻችን ናቸው። ችሎታዎችን ማጎልበት ፣ማልማት እንዲሁም በድርጅታችን እንዲቆዩ ማድረግ፡፡
እኛ ለደንበኞች ፍላጎት የላቀ መፍትሄዎችን የምናቀርብ የደንበኞች ማዕከላዊ/ደንበኞችን ማእከል ያደረግን ድርጅት ነን
ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በመተግበር ለምርጥ ልምዶች ተምሳሌት መሆን እንፈልጋለን

የኩባንያው ማንነት

“ሐበሻ” የሚለው ስም ለሲሚንቶ ኩባንያችን የተሰጠ ስያሜ ሲሆን የሚከተሉትን ትርጓሜ ያካትታል፤-

የመጀመሪያ ደረጃ ጥራት
ለምርጥ የደንበኞች አገልግሎት የሚተጋ
ሠራተኞችን መንከባከብ
ማህበረሰብ-አቀፍ ላይ የተመሠረተ የባለቤትነት መዋቅር
ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ምርቶች
ለማህበራዊ ሀላፊነት ተገቢውን ትኩረት መስጠት