ጌትስ ኢንተርናሽናል ሕንፃ 7ኛ ፎቅ
+251-114-16-32-73
ጌትስ ኢንተርናሽናል ሕንፃ 7ኛ ፎቅ

የድርጅቱ ማህበራዊ ሀላፊነት

የሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር ፋብሪካው ባለበት አካባቢ ማኅበረሰቦች ኢኮኖሚያዊ ፣ ማኅበራዊና አካባቢያዊ መረጋጋትን ማረጋገጥ ለንግድ ሥራው ጠንካራ እና የተሳካ እንደሚሆን በመርሕ ደረጃ በጥብቅ ያምናል ፡፡ የህብረተሰቡ ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ የሐበሻ ሲሚንቶ ጥንካሬ ነው፡፡ በዚህ ዋና መርህ በማመን፤ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ማህበራዊ ኃላፊነት ተግባራትን አከናውኗል ፣

የሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር የመአድን ቦታና የመፍጫ ቦታን ከጎሮ ከተማ የሚያገናኝ የ 10 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ ግንባታ
ጎሮ ከተማን ከጎሮ መንደር በሙገር አስፋልት መንገድ መገናኛ ጋር የሚያገናኝ 21 ኪ.ሜ. መንገድን ማሻሻል የ 40 ሚሊዮን ብር ወጪ
በሜታ ወልቂጤ ወረዳ የ 17 ኪ.ሜ ርቀት ያለው የህዝብ መንገድ ማሽኖቹን በመመደብ መጠገን ተችሏል ፡፡
የህዝብ ማመላለሻዎች የሚገለገሉበት የኖራ ድንጋይ ጥሬ እቃ ለማጓጓዝ የ 30 ኪ.ሜ ሸካራ መንገድን በመደበኛነት ይጠግናል
በፋብሪካው ዙሪያ ላለው ማህበረሰብ 100 በላይ አባወራዎችን እና የጎሮ ማኮ ጤና ጣቢያን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጀነሬተር ለጎሮ ማኮ የማህበረሰብ ጤና ጣቢያ 300,000 ብር በሚገመት ወጪ በእርዳታ አበርክቷል
በአምስት ወረዳዎች ለሚገኙ 12 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለ6000 ተማሪዎች ተደራሽነት ያለው ከ 2300 በላይ አጋዥ መጻሕፍት እና ሉሎች ልገሳ ለማድረግ ወደ 120000 ብር ወጪ ተደርጓል፡፡
በኢትዮጵያ ክረምት የሰብል ማሳዎቻቸው በጎርፍ ለተጥለቀለቀባቸው የወልመራ ወረዳ አምስት ቀበሌዎች ምርጥ የሽምብራ ዘር ተከፋፍሏል፡፡
በሜታ ወልቂጤ (ሱባ ጋጆ አከባቢ) ዙሪያ በጎማ ጥገና ንግድ ሥራ ለተደራጁ ሥራ አጥ ወጣቶች የተሟላ የቴክኒክ ሥልጠና እና የሥራ መሣሪያ ግዥ ያካተተ ወደ 100,000 ብር ድጋፉ ተደርጓል፡፡
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ግማሽ ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም ፊንፊኔ ዙሪያ በኦሮሚያ ልዩ ዞን የመቶ ሺ ብር እርዳታ ተደርጓል፡፡
በዲስትሪክቱ SME/የስራ እድል ፈጠራ ጽህፈት ቤት ለተደራጀ በጎሮ ዙሪያ ለ 33 ሥራ አጥ የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ወጣቶች ክሬሸር ተለግሷል፡፡ የድንጋይ መፍጫ ተከላ እና ሙሉ የቴክኒክ ድጋፍ ወደ 500,000 ብር ወጪ ተደርጓል፡፡

ከህብረተሰቡ በጣም አንገብጋቢ ፍላጎቶች ጋር ለመወያየት እና ለመፍትሔው ከተለያዩ  ባለድርሻ አካላት ጋር ያለማቋረጥ እንገናኛለን፡፡ ከዚህ ባሻገር አስፈላጊ እና ጠቃሚ ምክሮችን ከሚሰጡን የህብረተሰብ ሽማግሌዎች ፣ ሰራተኞች ፣ አማካሪ ቡድኖች ፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በንቃት እንሳተፋለን፡፡