ጌትስ ኢንተርናሽናል ሕንፃ 7ኛ ፎቅ
+251-114-16-32-73
ጌትስ ኢንተርናሽናል ሕንፃ 7ኛ ፎቅ

ሐበሻ ሲሚንቶ የኮርፖሬሽን አስተዳደር

ድምፅ የመስጠት ሀላፊነት ያለው የድርጅቱ ከፍተኛ የሥልጣን አካል ነው። ጠቅላላ ጉባኤው ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ በንግድ ሕጉ እና በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ የተሰጠው ሥልጣን አለው።

የድርጅቱን አቅጣጫ የመወሰን
በዓመታዊው የሥራ-አፈፃፀም ዘገባ ላይ የመምከር እና የማፅደቅ
የድርጅቱን የተመረመረ ዓመታዊ የሂሳብ ዘገባ የማፅደቅ
የካፒታል መዋቅሩን የመወሰን
የዳይረክተሮች ቦርድን እና ውጫዊ ኦዲተሮችን የመምረጥ

ቦርድ

የሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ ባለአክሲዮኖች በድርጅቱ አስተዳደር እና ሥራ አፈፃፀም ላይ ያላቸውን እምነት ከፍ የሚያደርግ እንደሆነ የሚያምንበትን ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለውን የኮርፖረሽን አስተዳደር ለመፍጠር የሚተጋ ነው። ቦርዱ፣ ኢንቬስተሮች የድርጅቱን የአስተዳደር እና የሥነ-ምግባር ግዴታዎች በተግባር ላይ የመዋል፣ ድርጅቱ ግዴታዎቹን እየተወጣ መሆን አለመሆኑን እና በዚያም ውስጥ ያሉ ኃላፊነቶቹንም መፈፀም አለመፈፀሙን፣ መገምገም የሚያስችላቸውን የኮርፖሬሽን አስተዳደር መዋቅር ለመመሥረት የሚሠራ ነው።

የሥራ አመራር ኮሚቴ

የድርጅቱ የዕለት ተዕለት የንግድ ሥራ እና የሥራ አፈፃፀም ጉዳዮች አባላቶቹ በዋና ሥራ አስፈፃሚው ለሚሰየሙት ለሥራ አመራር ኮሚቴው (Mancom) በውክልና ይሰጣሉ። ኮሚቴው ለሥራ ሂደት፣ ለፋይናንስ እና የመረጃ ቴክኖሎጂ፣ ለአቅርቦት ሰንሰለት፣ ለእቃ ግዢ፣ ለሽያጭ እና ለማስታወቂያ፣ ለሰው ኃይል ቁልፍ የሆኑ የንግድ ሥራ አገልግሎቶች ኃላፊነት ያለባቸውን ግለሰቦች ይይዛል። ኮሚቴው በየወሩ ወይም እንደአስፈላጊነቱ በተከታታይ የሚሰበሰብ ሲሆን፣ አጀንዳው በተለይ የሚያተኩረው በቦርዱ የፀደቁትን የሥራ አፈፃፀም ዓላማዎችን ከግብ በማድረስ ላይ ነው። እየታየ ባለው ዓመት ውስጥ፣ የሥራ አመራር ኮሚቴው፣ በፋይናንስ ዘገባው ላይ የተገለፀውን ከፍ ያለ የሥራ አፈፃፀም ለማስገኘት፣ ስምምነት የተደረገባቸውን የድርጅት እና የአገልግሎት ግቦች በመዘወር እና የቦርዱን ውሳኔዎች በመተግበር ሁነኛ መሣሪያ ነበር።

የሥራ አመራር ኮሚቴው ኃላፊነት

የተቋሙ ቦርድ የስራ መመሪያን መሰረት አድርጎ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የስራ አመራር ኮሚቴው ዓመታዊ በጀት እና ቢዝነስ ፕላን አዘጋጅቶ ለቦርድ ያፀድቃል፡፡ የውስጥ ጉዳዩችን በተመለከተ ደግሞ የስነምግባር ትግበራ እና ስራዎች የስልጣን ተዋረድን ጠብቀው እንዲሄዱ ማድረግ በኮሚቴው ቁጥጥር ስር ያሉ ጉዳዮች ናቸው

የአስተዳደር መዋቅር