የሽያጭና ስርጭት ዘዴዎች
ቀጥታ ሽያጭ
በዚህ የሽያጭ ስርዓት የሚስተናገዱት ደንበኞች ምርቱን በቀጥታ የሚጠቀሙ ሲሆን እንደ ኮንትራቸተሮች፣ የብሎኬት አምራቾች ቤት ገንቢዎች እና መሳሰሉትን ያካትታል፡፡
ተዘዋዋሪ የሽያጭ
በዚህኛው የሽያጭ ሰንሰለት ምርቶቹን እንደገና ለሚሸጡ ደንበኞችን የሚያገለግል ሲሆን እንደ አከፋፋዮች እና እንደ ቸርቻሪዎች ያሉ አካላት ይሳተፋሉ፡፡
የዲፖ የሽያጭ
ጃክሮስ አካባቢ በከፈትነው አዲስ ዲፖ ለሲሚንቶ/ለቡሉኬትና መሰል ምርት አምራቾች ተደራሽነት በመሆን በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶቹን እያቀረብን እንገኛለን፡፡ በመጋዘኑ አነስተኛ እና ከፍተኛው የግዢ መጠን በቅደም ተከተል በአንድ ግብይት 5 ቶን እና 20 ቶን ነው፡፡
ቀጥታ
በድርጅቱ መኪኖች ለደንበኞች በቀጥታ የማድረስ
በተዘዋዋሪ
በደንበኞች መኪና ከፋብሪካችን የማስረከብ አገልግሎት፤
የቴክኒክ ሽያጭ ድጋፍ
ደንበኞቻችን በምርት ጥራታችን ላይ ለሚያጋጥማቸው ጥያቄዎች ወይም ማንኛውም ተያያዥ ጥያቄ በቴክኒካዊ የሽያጭ ባለሙያዎቻችን በኩል ሊፈታ ይችላል፡፡ ባለሞያዎቻችን በደንበኞች የመስሪያ ቦታ በመገኘት የቴክኒክ ድጋፎችን ይሰጣሉ እንዲሁም ከምርትጋር ተያያዥ የሆኑ ቅሬታዎችን ያስተናግዳሉ፡፡
የክፍያ ስርአት
ሁሉም የሽያጭ ሂደቶች የሚከናወኑት በጥሬ ገንዘብ ላይ በተመሰረተ የሽያጭ ስርአት ሲሆን ክፍያ በ ሲፒዮ ፣ በቼክ ፣ በተቀማጭ ወረቀት/በባንክ ወደ ድርጅታችን ሂሳብ በመላክ ወይም በኤሌክትሮኒክ ሊከናወን ይችላል፤፤